ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአዲሱ የጋና ኘሬዝዳንት በዓል ሲመት ላይ ተገኙ፤

ጥር 01፣2009 ዓ.ም.

እ.ኤ.አ በታህሳስ 7 ቀን 2016 በተካሄደ ምርጫ ያሸነፉት የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ማሃሙዱ ባውሚያ በጋና መዲና አክራ ውስጥ ቃለ መሀላቸውን ፈጽመዋል።

በቃለ መሃላ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የ11 አገራት መሪዎችና ከስድስት ሺህ በላይ ጋናዊያን ታድመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የምርጫ ሂደቱን "ለአፍሪካ አገሮች ተምሳሌት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አካሂዳለች። ሌሎች አፍሪካውያንም ዱካውን የምንከተለው ይሆናል" በሚል ገልጸውታል።

ጋና እና ኢትዮጵያ "የበለጸገች፣ አንድነቷን የጠበቀች አፍሪካን ለማየት የጋራ ራዕይ አላቸው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፤ በጋና የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ተመልሰዋል።