ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጤና ትርኢት እና ኮንፈረንስ ልታስተናግድ ነው፤

ጥር 2፡2009 ዓ.ም.

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 13-15/2017 የጤና ባለሙያዎች ልምድ ይቀያየሩበታል የተባለ ዓለም አቀፍ የጤና ትርኢት እና  ኮንፈረንስ  ለታስተናግድ ነው።  የኮንፈረንሱና የትርኢቱ አዘጋጅ እና የሜዲኮ-የባዮ-ሜዲካል ኮሌጅ ፕሪዚዳንት የሆኑት ዶ/ር መኮንን ሃጎስ እንዳሉት በዝግጅቱ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች እና መድሃኒቶች ለትርኢት የሚቀርቡበት ነው ብለዋል። አዘጋጁ አክለው ትርኢቱ ቴሌ-ሜዲስን የተባለ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምን ቴክኖሎጂን ያስተዋውቃል ብለዋል። ኢትዮጵያውያን እንደ ህንድ ወይም ታይላንድ ባሉ አገራት ለህክምና የሚያወጡትን ወጪ አስታውሰው፣ ኢትዮጵያ በጤና ቱሪዝም ያለውን ያልተነካ ኃብት መጠቀም ከቻለች ከፍተኛ ጥቅም ልታገኝ ትችላለች ብለዋል ዶ/ር መኮንን ሃጎስ።