ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ትብብር እንዲኖራት ጥሪ አቀረቡ፤

ጥር 02፣2009 ዓ.ም.

የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በኢትዮጵያ የሀገራቸው አምባሳደር በሆኑት ማዳም ፋቱማታ ካባ በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በላኩት መልእክት በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈረሙት ስድስት ስምምነቶችን ተግባራዊ በማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ማሳደግ እንደሚፈልጉ  በመልእክታቸው ገልፀዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው የተፈረሙ ስድስት ስምምነቶችን ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪ የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን አላማ ያደረገ  ኢትዮጵያ ያላትን ምርጥ ተሞክሮ ለጊኒ ለማካፈል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል::