መካከለኛው ምስራቅ

አገራችን የምትገኝበት መልከአምድራዊ አቀማመጥ  ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ያለንን ትስስር ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፤ ከክፍለ ዓለሙ ጋር ከፍተኛ የሆነ የታሪክ፣ የባህል፣ የሀይማኖት እና ቋንቋ ግንኙነት አለን፡፡ ሆኖም ከአካባቢው አገራት በተለይ ከግብጽ ጋር ያለን ግንኙነት የዓባይ ወንዝ ፍትሀዊ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ችግሮች የነበሩበት ሲሆን፤ በዚህ እና አገራችንን እንደ ሙሉ በሙሉ የክርስቲያን አገር አድርገው በሚቆጥሩ አንዳንድ የአረብ አገራት ጋር ጥርጣሬ የተሞላበት ግንኙነት የነበረን መሆኑ ይታወቀል፡፡  በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች  ክልሉ በልማት እና የዲሞክራሲ ግንባታችን ለይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡  በመሆኑ በክልሉ የምንከተለው ፖሊሲ ይህንኑ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡  በተጨማሪም ከክልሉ ጋር ሊኖረን የሚገባው ግንኙነት ግጭቶችን በማስወገድ ላይ የተመሰረተ እና በሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አኳኋን የሚመራ መሆን ይኖርበታል፡፡