ከዩናይትድስቴትስ ጋር የሚኖረን ግንኙነት

ከዩናይትድስቴትስ ጋር የሚኖረን ግንኙነት  ከአውሮፓ ሕብረት አገራት ጋር ከሚኖረን ግንኙነት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፤ በዋናነት ግን  አሜሪካ በዓለም ላይ ካላት የመሪነት ሚና ጋር አብሮ የሚሄድ መሆን አለበት። በተጨማሪም በዓለም ላይ ያለች የትልቅ ኢኮኖሚ የሚ ባለቤት በመሆኗ ወሣኝ ዓለም አቀፍ ሕግጋጋት የምታወጣ እንደመሆኑ መጠን የአሜሪካ ድጋፍ ማግኘት ለልማታችን እና ለብሔራዊ ደህንነታችን ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ከፍ ከማድረግ አኳያ ሊረዱ ከሚችሉ ጉዳዮች አንዱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊና ትውልድ ኢትዮጵያዊ በአሜሪካ መገኘት ነው። ይህን እምቅ ሀብት በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ የሁለቱን አገሮት ግንኙነት ለማዳበር ትርጉም ያለው ሚና ሊጫወት ይችላል። በተጨማሪም ሀገራችን ለዲሞክራሲ ለልማት ለአካባቢያችን ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የሚደረገው ጥረት በአሜሪካ ዘንድ በበጎ አይን የሚታይ በመሆኑ የሀገሪቱን ድጋፍ ሊያስገኝልን ይችላል።ባጠቃላይ ከአሜሪካ ጋር የምንከተለው ፖሊሲ በአገሪቱ ያሉትን የገበያ እድሎች መጠቀምን ጨምሮ  ከአሜሪካ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ልናገኝ የምንችለውን የልማት ብድር እና እርዳታ በማሣደግ ላይ የተመሰረተ መሆን  አለበት።